ውሾች ከአቦሸማኔ ጋር ለመወዳደር አንድ ላይ ተሰባስበው ግቡ የትኛው ፈጣን እንደሆነ ለማወቅ ነበር።
አቦሸማኔው ካለበት ቦታ አለመውጣቱ ሁሉም ተገረመ። የሩጫውን አስተባባሪ ምን ተፈጠረ ብለው ጠየቁት!?
ይህንን ምስል ካየ በኋላ የሰጠው ምላሽ፡-
"አንዳንድ ጊዜ ምርጥ መሆንህን ለማረጋገጥ መሞከር ስድብ ነው።"
እኛ በጣም ጠንካራዎች መሆናችንን እንዲረዱ ወደ ሌሎች ሰዎች ደረጃ መውረድ አያስፈልገንም።
በደንብ አስብ እና ጉልበትህን ለሚገባህ ነገር አስቀምጥ።
አቦሸማኔው ፈጣን እና ጠንካራ መሆኑን ለውሾች ለማረጋገጥ ሳይሆን ለማደን ፍጥነቱን ይጠቀማል።
ምንም ዋጋ በሌላቸው ነገሮች ጊዜህን እና ጉልበትህን አታባክን።